ይድረስ ለጠ/ሚንስትር ዶ/አብይ አህመድ፣ ለብልጽግና መንግስት ኃላፊዎችና የካቢኔ አባላት
ይህን ጽሁፍ በይፋ እንድጽፍ ያነሳሳኝ፣ሀገራችን ከኣንድ ቀውስ ወደ ሌላ ቀውስ፤ ከአንድ ፈተና ወደ ሌላ ፈተና እየተሸጋገረች የምትሰቃይበት ምክንያቶች አንዱ በተፈጥሮዋ ወይም በሕዝቦቿ አለመታደል ሳይሆን፤ በዋነኛነት የሚመራዉን ሕዝብ አስተባብሮ በመምራት ችግሮቿን ከስር ነቅሎ የሚጥልላት ፈውስ የሚሆኑ አስተውሎ ያላቸው መሪዎች እስከዛሬ ባለማግኘቷ ነው ብየ ስለማምን ነው። ይህ ለዉጥ ሲጀምር በብዙ ሚልዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያዉያን በዶ/ር ዓብይ ላይ እምነት በመጣል አሁን ሊያልፍላት ነው፤ መሪ እያገኘች ነው ብለው ነበር፤ለኢትዮጵያ ጥሩ ራይ ሰንቀው ለውጡን በስተመጨረሻም ቢሆን የተቀላቀሉትና የተራራውን ጫፍ የወጡት ዶ/ር አብይ፣ የኢትዮጵያ ህዝብ ከፍተኛ ክብርን፣ ድጋፍ (እኔም በርካታ የትግል ጓዶቼን ጨምሮ) ሲያደርጉ ቆይተዋል። አሁን ግን ያ ተስፋ እኔን ጨምሮ በብዙ ወገኖች ዘንድ እየተመናመነ የመጣ ይመስላል::
Read More